X

By ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ
Fri, 06-Dec-2019, 09:10

እፀ መሰውር

ሰላም የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቤተሠቦች ስለ እፀ መሰውር 

ይዘን ቀርበናል መልካም ንባብ!!!

እፀ መሰውር 

በሀገራችን ኢትዮጵያ ቀደምት አባቶቻችን ከሚጠቀሙባት የጥበብ እፅ አንዷ እፀ መሰውር ትባላለች ይህች እፅ ከዚ በፊት በከፊል ለመመልከት እንደሞከርነው አንድን ነገር ከሰው ልጅ ዕይታ መሰወር የተፈጠረችበት ተግባሯ ነው። በኢትዮጵያ ሀገራችንም ወይናደጋ በሆኑ አካባቢዎችና በተራራማ ቦታዎች ላይ እፅ መሰውር እንደምትገኝ ይነገራል። እግዚአብሔር ሄኖክን በስተምስራቅ በኤዶም ገነት አካባቢ ካሳየው በርካታ አፀዋቶች መካከል አንዷ እፀ መሰውር ናት ይህችም እፅ ቀደምት አባቶቻችን ከመፅሀፈ ሄኖክ ወስደው መፍትሄ ሥራይ ተብሎ የሚጠራው መፅሀፍ ላይ በብራና ፅፈዋት ዘርፈ ብዙ ስራዎችንም ሰርተውባታል ለምሳሌ አባ ተስፋስላሴ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው የተዋህዶ አንበሳ ክርስቶስ ነው በሚለው መፅሐፍ ላይ እንደገለፁት በርካታ ቤተመንግስቶች በከበሩ እንቁ ያጌጡ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት የቴክኖሎጂ ከተሞች እንዲሁም ጠበብት አባቶች ብራና ፍቀው ቀለም በጥበጠው በሀረግ አስውበው የፃፉልን ቅዱሳት መፃህፍትን በአደራ መልክ የያዙ ግዙፍ ፒራሚዶችን አባቶቻችን በዝች እፀ መሰውር በተባለች እፅ ሰውረው አስቀምጠዋቸዋል። በአባዛኛው የኢትዮጵያ የገጠር ማህበረሰብ አካባቢ በተደጋጋሚ የእጣን ሽታ እዚ አካባቢ ይሸታል ሌሊት ሌሊት ከበሮ ሲመታ ይሰማል የፅናፅን ድምፅ ሰማን የሚሉ አያሌ ናቸው እነዚህ አካባቢዎች ስውር ቤተመቅደስ ያላቸው አካባቢዎች እንደሆኑ አባቶች ይናገራሉ።


ዛሬ በአለም ከፍተኛ አይምሮውን የተጠቀመ ሰው 0.001% እንደሆነ ይነገራል ነገር ግን ያለንበትን ስልጣኔ ተመልከቱት ያደጉ ሀገራትን የከተሞቻቸውን ውበት ተመለከቱት የሰው ልጅ ይችን ፐርሰንት አይምሮውን ተጠቅሞ ይህን ሁሉ ነገር ከሰራ 100% ቢጠቀም ምን ሊሰራ ይችል ይሆን???? ልብ በሉ አይምሮውን 100% የተጠቀመ ሄኖክ ኢትዮጵያዊ በዚህ አለ። አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረጉ የጥበብን ጥግ የእወቀትን ስፋትና ቁመት የለካ ጠቢብ ሄኖክ አለ እንግዲ አባቶቻችን ስውር ከተሞችን ቤተመንግስቶችን ፒራሚዶችን የሰሩት ከሄኖክ በወሰዱት ጥበብ ነው ምን ያህል የረቀቀ ከተማ ሊሆን ይችላል? ምን ያህል የተዋበ ቤተመንግስቶችን ሊሰሩ ይችላሉ? ይህን ለመረዳት አይቻልም።

ታድያ ይቺ መሰወር በምን ዓይነት መንገድ ነው ነገሮችን ከዕይታ ውጪ የምታደርገው የሚል ሀሳብ ሊነሳ ይችላል ነገር ግን አባቶቻችን ዳዊት ደግማችሁ እፅን አትንኩ ማለታቸው ለምን እንደሆነ ልብ እንድንል ያደርገናል ከመዝሙረ ዳዊት አንድ የተመረጠ ምዕራፍ ይደገምና ይህችን እፅ ትቆረጣለች መዝሙረ ዳዊትን የደገመው አካል ይህችን እፅ በመጠቀም ከእይታ መሰወር  የሚፈልገው ነገር ይሰውርባታል።

አባቶቻችን ይህን የመሰለ ብዙ የጥበብ ነገርን ተጠቀሙ እጅግም ኢትዮጵያዊነትን አገነኑ  ዛሬ ግን ታሪክ ሰሪ ሳይሆን ታሪክ አጥፊ ትውልድ ተፈጠረ የጠቢበኞቹ ልጅ መርገም ሆኖ አረፈው ታሪክ መስራቱ ይቅርና የአባቶችን ታሪክ እንኳ መጠበቅ ተሳነው እሳት አመድን ወለደ ማለት ታድያ ይህ አደለም? እኛ ማለት የቀደሙት የእሳት ትውልድ  ልጆቻቸው አመዶች ነን አዎ እሳት አመድን ወልዷል።

 መልካም ምሽት

***********************************

ትክክለኛ ቻናሎች እነዚህ ናቸው

????????

• የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቻናሎች - 

? YouTube channel - Subscribe it now, thanks ❤️

namrud pictures & short films -https://youtube.com/channel/UCCW7MBWOARd2N_xupBoJAxw/videos

? የቴሌግራም ቻናላችን- አሁኑኑ join ያድርጉ 

@RAFATOEL_ZETHIOPIA

(https://t.me/RAFATOEL_ZETHIOPIA)

?የፌስቡክ ገጻችን- አሁኑኑ Follow/Like  ያድርጉ 

ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ (https://m.facebook.com/ራፋቶኤል-ዘኢትዮጵያ-112582176799540/?tsid=0.7487612614507868&source=result)

?በኢንስታግራም አድራሻችን follow 

https://www.instagram.com/Rafatoelzethiopia/

?በድረገጻችን 

https://rafatoelzethiopia.websites.co.in

Follow, subscribe እና join ያድርጉ እናመሰግናለን

??????????


ሀሳብ አስተያየታችሁን

????????

 @Rafatoel_bot     

r*****************@g*****.com

????????


This site was designed with Websites.co.in - Website Builder

WhatsApp Google Map

Safety and Abuse Reporting

Thanks for being awesome!

We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!

Have a great day!

Are you sure you want to report abuse against this website?

Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support