X

By ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ
Fri, 29-Nov-2019, 18:35

አክሱም ሐውልት


ሰላም የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቤተሠቦች ስለ አክሱም ሐውልት

ይዘን ቀርበናል መልካም ንባብ!!!

አክሱም ሐውልት

አክሱም ሐውልት ከ1700 አመታት በፊት እንደተሰራ የታሪክ በዛግብት ይናገራሉ። ይህ ሐውልት በአይነቱ ለየት ያለ ቅርፅን የያዘ ሲሆን በአሁን ሰአት ለአርኪዎሎጂስት አጥኚዎች ጥያቄ የፈጠረባቸው በዛ ስለጣኔ ባልነበረበት ዘመን እንዴት ይህን ግዙፍ ሐውልት ቀረፀው አቆሙት የሚል ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ብዙ መላምቶች ይቀርባሉ ከነሱም ውስጥ አንዱ አክሱም ሀውልት አባቶች ያቆሙት በዝሆን ጎትተው ነው የሚል የተሳሳተ የአጥኚዎች አስተሳሰብ ነው። 

ሆኖም ይህን አስተሳሰብ ብንቀበል እንኳ አሁንም ድረስ የአክሱም ሐውልት የኢትዮጵያን ቀደምት ስልጣኔ ፍንትው አደርጎ ያሳያል።

ዘመናዊ መሳሪያና መለኪያ በሌለበት ዘመን የዘመኑ ሕንፃ ባለሙያዎች በቀላሉ ሊሰሩት የማይቹሉትን ልኬትና ቅርፅ ጠብቀው ድንቅ የሆነ የጥበብ አሻራቸውን አባቶቻችን አስቀምጠዋል።

አክሱም የጥበብ መሠረት የስልጣኔ ምንጭ የኢትዮጵያዊነት ጥበብ ድብቅ ምስጢር ነው ጣልያን ይህ ቢገባት ነው ነቅላ ወስዳ በሮም አደባባይ ያቆመችው። አክሱም ይህ ስፈራ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ፅዮን ማርያም ቤተክርስቲያን ያለችበት ቦታ ነው በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥም የመጀመሪያዋ ሙሴ ከእግዚአብሔር የተቀበላት አስርቱ ትዕዛዛት የተፃፈባት ፅላት ዘመሴ ተብላ የምትጠራው የታቦተ ፅዮንም መናገሻ ነው። ስለ ታቦተ ፅዮን በሌላ ጊዜ የምንዳስሰው ሲሆን አሁን ግን ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስና አክሱም ሀውልት ከአንድ ወጥ አለት ድንጋይ ተፈልፍሎ የቆመ ሲሆን ከላይ እንደጠቀስነው እንዴት ተፈለፈለ ማን ፈለፈለው ለምን ተፈለፈለ እንዴት ቆመ ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመሴጠት ከአይምሮ በላይ ይሆናል ምክንያቱም ያን ጊዜ ቴክኖሉጂ የለም ብረት አቅልጠው በመዶሻና በብረት ቀጥቅጠው ካልፈለፈሉት በቀር በየትኛው ማሽን ሊፈለፈል ይችላል? ብለን ካሰብን ትልቅ ስህተት ይሆናል አባቶቻችን ይህንን ሐውልት ጎትተው አላቆሙትም ቀጥቅጠውም አልፈለፈሉትም ይልቁንም በእጃቸው የነበረውን መፅሐፈ ሄኖክን ተጠቅመው አነፁት እንጂ። 

መፅሐፈ ሄኖክና አክሱም ሐውልት ምን አገናኘው ትሉኝ ይሆናል ነገር ግን መፅሐፈ ሄኖክን የጠቀስኩበት ምክንያት ወደ ማስረዳት ልሂድ።

ሄኖክ ክፍጠረት ሁሉ ያላየው ያልጎበኘው የለም እግዚአብሔር ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ለሄኖክ ያላሰየው የለም ታድያ እነዚህ ካያቸው ነገሮች መካከል የጥበብ እፅዋት ማዕድናትና የከበሩ ደንጋዮች ይካተቱበታል ከከበሩት ማዕድናት መካከል አንዱ ደንጋይን የማቅለጥ ሀይል ያለው ማዕድን እንደነበረና ይህ ማዕድንም በኢትዮጵያ ብቻ እንደሚገኝ አባቶች ይናገራሉ። ታድይ አክሱም ሀውልት ቅርፁን ሳይለቅ በዝሆን ሳይጎተት አባቶቻችን በበልሀት የቀረፁት በዚህ ድንጋይን በሚያቀልጥ ማዕድን እንደሆነም ፀሀፍት አባቶች ይናገራሉ። 

አክሱም ሐውልት ለምን ይጠቀሙበት ነበረ?

አክሱም አካባቢ ከፍተኛ የሆን ስልጣኔና የንግድ ስራ በስፋት የነበረበት ሲሆን ከተለያዩ አለማት ነጋዴዎች ወደዚህ ስፍራ በመምጣት የንግድ ስራቸው ያጧጡፉ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ይናገራሉ።

ታድያ እነዚህ ከተለያዩ ክፍል ዓለማት የሚመጡ ነጋዴዎች በምሽትም ሆነ በቀን ወደ አክሱም ለመምጣት አይቸገሩም ነበረ። እንዴት ያላችሁኝ እንደሆነ ነገሩ እንዲህ ነው።

አክሱም ሐውልት አትኩረን ስንመለከተው ከላይ ክቧ ጋር የተበሳ ቀዳዳ ነገር አለ ይህ ቀዳዳ በዛን ዘመን አንድ የከበረ ማዕድን ነበረው ይህ ማዕድን ቀን የፀሀይ ብርሀንን በመሰብሰብ ማታ ማታ ለአካባቢው ደማቅ የሆነ የተለያየ ቀለም ያለው ብርሀንን ያወጣ ነበረ። ታድያ ይህን ያሸበረቀ ቀለም ቀሩቅ ሆነው የሚመለከቱ ነጋዴዎች በቀላሉ ወደ አክሱም ለመምጣት ይረዳቸዋል ለከተማዋም እንደ መብራትነት ያገለግል ነበረ። ይህ ማዕድን አባቶች አውርደው እንደደበቁት የሚናገሩ አሉ አንዳንዶቹም ግራኝ አህመድ ወስዶት ነው ይላሉ ዮዲት ጉዲት ናት የወሰደችውም የሚሉ አሉ ነገር ግን ግራኝ አህመድ ከወሰደው ወዴት አደረሰው?? ዮዲት ጉዲትስ ወዴት ሸሸገችው?? ብለን ስንጠይቅ አባቶች አውርደው ደብቀውታል ወደሚለው ያመዝንብናል። 


              የአክሱም ሐውልት  ቅርፅ

የአክሱም ሐውልት ቅርፅ የወንድ ልጅን ብልት የሚመስል ሲሆን በዚህም አምሳል የተሰራበት ምክንያት ቀደምት ኢትዮጵያውያን በአምልኮተ እግዚአብሔር የነበሩ በአንድ አምላክ የሚያምኑ አብርሃማውያን በመሆናቸው አብርሃም አባታችን ብለው ያምኑም ስለነበረ በኦሪቱ ስርአት የአብርሀም ዘር የአንድ አምላክ አማኞች መገረዝ ግዴታቸው ነበረ ያልተገረዘ የአብርሃም ዘር አደለም ስለሚባል ልክ በሐዲስ ኪዳን ያልተጠመቀ ክርስቲያን እንደማይባል ሁሉ በኦሪቱም ያለተገረዘ እንደዛው ነው ስለሆነም የአብርሀም ዘር ነን በእግዚአብሔር እናምናለን ሲሉ ኢትዮጵያውያን የተገረዘ የወንድ ልጅ ብልት ቅርፅ አድርገው አክሱምን አቁመውታል ከሩቅ የሚመለከቱት ነጋዴዎች ስደተኞች ሁሉ ይህ ስፍራ ማረፊያቸው ነበረ። በሐውልቱም ላይ ብዙ ምስጢራዊ የሆኑ ምልክቶችና መልዕክቶች አስፍረውበታል።

በአጠቃላይ አክሱም የምስጢሮች ሁሉ ቁልፍ ናት እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያ ሀገራችንን ይባርክ።

 መልካም ምሽት

***********************************

ትክክለኛ ቻናሎች እነዚህ ናቸው

????????

• የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቻናሎች - 

? YouTube channel - Subscribe it now, thanks ❤️

namrud pictures & short films -https://youtube.com/channel/UCCW7MBWOARd2N_xupBoJAxw/videos

? የቴሌግራም ቻናላችን- አሁኑኑ join ያድርጉ 

@RAFATOEL_ZETHIOPIA

(https://t.me/RAFATOEL_ZETHIOPIA)

?የፌስቡክ ገጻችን- አሁኑኑ Follow/Like  ያድርጉ 

ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ (https://m.facebook.com/%E1%88%AB%E1%8D%8B%E1%89%B6%E1%8A%A4%E1%88%8D-%E1%8B%98%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-112582176799540/?tsid=0.7487612614507868&source=result)

?በኢንስታግራም አድራሻችን follow 

https://www.instagram.com/Rafatoelzethiopia/

?በድረገጻችን 

https://rafatoelzethiopia.websites.co.in

Follow, subscribe እና join ያድርጉ እናመሰግናለን

??????????


ሀሳብ አስተያየታችሁን

????????

 @Rafatoel_bot     

r*****************@g*****.com

????????

This site was designed with Websites.co.in - Website Builder

WhatsApp Google Map

Safety and Abuse Reporting

Thanks for being awesome!

We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!

Have a great day!

Are you sure you want to report abuse against this website?

Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support