X

By ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ
Thu, 28-Nov-2019, 05:12

ንጉሥ ቶዎድሮስ(ቴ) 

ሰላም የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቤተሠቦች ስለ ሣልሳይ ቶ(ቴ)ዎድሮስ እንደ ቃላችን ይዘን ቀርበናል መልካም ንባብ!!!

ቶዎድሮስ(ቴ) ይህ ንጉሥ በብዙ ድርሳናት ላይ የቅዱሳን የትንቢት መፅሀፍ ላይ 

በሰፍት የተተነበየለት ንጉስ ነው ሳልሳዊ ቴ የእርሱ መለያ ምልክት ናት።

አንዳንዶች ይህ ንጉስ አዲስ የሚወለድ ከዛም በገዳም አባቶች ተቀብቶ ተባርኮ የሚነግስ ንጉስ ነው ብለው ሲናገሩ አንዳንዶች ደግሞ አይ ሳልሳዊ ቶዎድሮስ (ቴ) የንግስና ስሙ ነው እንጂ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊነግስ የሚመጣው ቅዱስ ናአኲቶለአብ ነው በማለት ይናገራሉ። 

ይህ ፃድቅ የእግዚአብሔር ሰው ሞትን ሳያይ ወደ ብሔረ ህያዋን የተነጠቀ እንደሆነ ገድሉ እና የተለያዩ ቅዱሳት መፃህፍት ያወሳሉ በመጨረሻ ዘመን ወደዝች ምድር ተመልሶ እንደሚመጣም ገድሉ ይናገራል። ከዚህም በመነሳት ሳልሳዊው ንጉስ ናኲቶለአብ ናቸው ተብሎ ይታመናል።


ሳልሳዊው ንጉስ የሚመጣው የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለመግለጥ ነው። ጌታችን በወንጌል እንደተናገረው በመጨረሻ ዘመን ብዙ መከራ ረሀብ ጦርነት እንደሚመጣ ቀኖቹ ባያጥሩ ስጋ የለበሰ ሁሉ የማያተርፍበት ዘመን እንደሆነ ተናግሯል ታድያ ይህ የመከራ ዘመን ኢትዮጵያ ላይ ህዝቡ በርትቶ ከፀለየ ለሦስት ወር ከዛም አልፎ ተግቶ ከፀለየ ለሦስት ቀን እንደሚሆን። ልባቸው ከደነደነ ግን ለሦስት አመት እንደሚሆን መፅሐፈ ሳቤላ ይናገራል። ኢትዮጵያ ላይ እንክርዳዱና ስንዴው የሚለየው በዝች አጭር ጊዜ ነው አርቴፊሻሉ ትውልድ አመድ የሚሆነው በዚህ ጊዜ ነው ይህን የመከራ ዘመን የሚያልፉት ንሰሐ የገቡ ብቻ እንደሆኑ ፍካሬ ኢየሱስ ይናገራል። ታድያ ንፁህ ኢትዮጵያውያን ብቻ ተለይተው ከቀሩ ከሶስት አመት በኋላ ሳልሳዊው ንጉስ ይመጣል። ይህ ንጉስ በእጁ ቶ በስቀልን የያዘ ነው። በመጨረሻም የአዳምን በትረ ንግስና የሆነችውን ቆ በትርን ካለችበት አውጥቶ ስውር አብያተ ክርስቲያናትን ረቂቅ የቴክኖሎጂ ስውር ከተሞችና ፒራሚዶችን ሁሉ እንደሚገልጥ የተቃጠሉትን የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት በወርቅ በእንቁ እያሸበረቀ እንደሚያድሳቸው በእርሱ የንግስና ዘመን እንኳን የሰው ጠማማ የእንጨት ጠማማ እንደማይኖር መፅሐፍቶቻችን ይናገራሉ። ታድያ ለሶስት አመት የኢትዮጵያ የጭንቅ ዘመን እንዳበቃ ንጉሱ ሲገለጥ የአለም መከራ ወይም ዘመነ አርማጌዶን እንደሚሆን የአለም ጭንቅ እንደሚጀምር ይነገራል በአለም ያሉ ኢትዮጵያን የናቁ ሁሉ ያኔ ይቅር በይን ይላሉ ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ይሻሉ። አለም በሰራቻቸው ቴክኖሎጂ እራሷ ትጠፋበታለች ያቆመቻቸው ሚሳኤሎች ሁሉ ምድሪቶን ምድረ በዳ ያደርጓታል ፊተኛ የነበሩት ሁሉ ኋለኛ ይሆናሉ ኋለኛ የሆነችው ኢትዮጵያ ደግም በከፍታ ማማ ላይ ሆና ቁልቁል ትመለከታቸዋለች። ሁሉ ይናፍቃታል የናቃት ሁሉ አግሯ ስር ይደፋል።

   ሳልሳዊው ቶዎድሮስ ቴ  የንግስናው ዘመን አርባ አመት ብቻ ነው በአርባኛው አመት አፈር ነውና አፈርን መቅመስ ስላለበት ከሩጫው ሁሉ ያርፋል። ያኔ ድጋሜ በመላው አለም የጭንቅ ቀን ይመጣል ሳጥናኤል በግልጥ በእራሱ አካል ምድርን ያስጨንቃታል የሚካኤልና የዘንዶው ጦርነትም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ይሆናል ዘንዶውም ድል ተነስቶ ወደ ጥልቁ እስኪጣል ግን በራዕይ ዮሐንስ የተፃፈውን የጥፋት ርኩሰት ሁሉ ይሰራል። በዚህ ጊዜ ሁለቱ የብሔረ ሕያዋን ታላላቅ ሰዎች ሄኖክና ኤልያስ ሞትን ለመቅመስ ይመጣሉ ኤልያስ በእሳት ሰረገላው ይወርዳል ከዘንዶው ጋር ይዋጋሉ ቅዱሳንን ሁሉ ድል ይነሳቸው ዘንድ ስልጣን ተሰጠው እንደተባለ ቅዱሳንን ድል ያረጋቸዋል ራእይ 13 (Revelation)

5፤ ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።

6፤ እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።

7፤ ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።


በመጨረሻም ዘንዶው ወደ ጥልቁ ይወረወራል ወደ ዘላለም የእሳት ቦታ ወደ በርባኖስ ይወድቃል ሰማይና ምድርም ያልፋሉ ሰዎችም ሁሉ በደመና ይነሳሉ ያኔ የሰው ልጅ የአማልክት አምላክ የንጉሶች ንጉስ በነጩ ዙፋን ላይ ተቀመጦ ከቶም ሊቆጠሩ በማይችሉ መላእክት እየተመሠገነ በሰማይ ይታያል። 


በቀጣይ ከንጉሱ ቶዎድሮስ ቴ ጋር አብሮ ስለሚመጣውና ፓትርያርክ ስለሚሆነው ብዙ ገቢረ ተአምራትን ስለሚያደርገው አባት እናወራለን መልካም ጊዜ።

 መልካም ዕለተ ሐሙስ

***********************************

ትክክለኛ ቻናሎች እነዚህ ናቸው

????????

• የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቻናሎች - 

? YouTube channel - Subscribe it now, thanks ❤️

namrud pictures & short films -https://youtube.com/channel/UCCW7MBWOARd2N_xupBoJAxw/videos

? የቴሌግራም ቻናላችን- አሁኑኑ join ያድርጉ 

@RAFATOEL_ZETHIOPIA

(https://t.me/RAFATOEL_ZETHIOPIA)

?የፌስቡክ ገጻችን- አሁኑኑ Follow/Like  ያድርጉ 

ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ (https://m.facebook.com/%E1%88%AB%E1%8D%8B%E1%89%B6%E1%8A%A4%E1%88%8D-%E1%8B%98%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-112582176799540/?tsid=0.7487612614507868&source=result)

?በኢንስታግራም አድራሻችን follow 

https://www.instagram.com/Rafatoelzethiopia/

?በድረገጻችን 

https://rafatoelzethiopia.websites.co.in

Follow, subscribe እና join ያድርጉ እናመሰግናለን

??????????


ሀሳብ አስተያየታችሁን

????????

 @Rafatoel_bot     

r*****************@g*****.com

????????

This site was designed with Websites.co.in - Website Builder

WhatsApp Google Map

Safety and Abuse Reporting

Thanks for being awesome!

We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!

Have a great day!

Are you sure you want to report abuse against this website?

Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support