ወድ የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቤተሰቦች
በኢትዮጵያ፣ ዛሬም ውቅር አብያተ ክርስቲያን ከወጥ አለት ተፈልፍለው እየታነፁ ነው – ቢቢሲ
ላሊበላን የመሰሉ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያውያን እየተደገሙ ነው፤ በሰ/ወሎ ዋድላ ወረዳ፣ አራት ውቅር መቅደሶች ከወጥ አለት ተፈልፍለው ታነፁ፤ ሐናፂው፣ ዘመናዊ መሣሪያ አይጠቀሙም፤የምሕንድስና ትምህርትም የላቸውም፤ “ጥበቡ የፈጣሪ ነው፤እኔ የእርሱ መሣሪያ ነኝ፤”/ሐናፂው አባ ገ/መስቀል ተሰማ/ “ከ800 ዓመት በፊት የሠሩትን ታሪክ በራሳቸው እጅ ደግመውታል፤” /ቢቢሲ/
†††
ከአንድ ወጥ አለት ተፈልፍለው የተሠሩት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን፣ በኢትዮጵያም ኾነ በዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ዘንድ በታሪካዊነታቸው ጎልተው ይታወቃሉ፡፡ አብያተ ክርስቲያኑ፣ በጠቢባን እጆች የተሠሩት ወይም የተፈለፈሉት፣ በ12ኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡ ይኹንና የእኒያ ጠቢባን እጆች ሥራቸውን ቀጥለውበታል፤ ዛሬም፣ ዐዲስ አብያተ ክርስቲያን በሀገራችን ጠቢባን እጅ እየተፈለፈሉ ናቸው፡፡
አባ ገብረ መስቀል ተሰማ ይባላሉ፤ ዐዲስ ሕንፃ አብያተ ክርስቲያን ከወጥ አለት በመፈልፈል ጥበብ የተካኑ ናቸው፡፡ አብያተ ክርስቲያኑን ፈልፍለው ለመጨረስ አራት ዓመት ፈጅቶባቸውል፡፡ ሥነ ሕንፃውም፣ እርሳቸው ምን ያህል በጥበብ የተሞሉ መኾናቸውን ያሳያል፡፡
“ኢትዮጵያውያን በዚያ ጥንት ዘመን ዘመናዊ መሣሪያ ሳይታጠቁ እንዴት ላሊበላን ያህል ቤተ መቅደስ ከአለት ወቅረው ቤተ ክርስቲያን ይሠራሉ?” የሚል ጥያቄ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲነሣ ቆይቷል፤ ጥያቄውን ይዘው፣ “የጥበቡ ባለቤት ሌላ ነው፤ ከሀገሪቱም ውጭ ነው፤” ወደ ማለት ያመሩ አሉ፤ “የሚሠሩም ከኾነ እስኪ ይድገሙት፤” ያሉም አልጠፉም፡፡
ዓለም አቀፍ ሚዲያ የኾነው ቢቢሲ፣ “በዩኔስኮ የተመዘገቡ የቅርስ ሥፍራዎችና የብዙኃን ጎብኚዎች መዳረሻ የኾኑት ኢትዮጵያውያን፣ ከ800 ዓመት በፊት የሠሩትን ታሪክ በራሳቸው እጅ ደግመውታል፤” የሚል ሐሳብ ያለውን ዘገባ አውጥቷል፡
“ዳግማዊ ላሊበላ” የሚል ስያሜ የተሰጣቸው አብያተ ክርስቲያኑ፣ በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ከጋሸና ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ ለላሊበላ ከተማ ቀረብ ባለ ሥፍራ ነው እየታነፁ ያሉት፡፡ ቢቢሲ ታዲያ፣ “በጥልቀትም ኾነ በጥበብ መገለጫ የሌላቸው ላሊበላን የመሰሉ ውቅር አብያተ ክርስቲያን በኢትዮጵያውያን እየተደገሙ ነው፤” የሚል መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡
“ጥበቡ የፈጣሪ ነው፤ እኔ የእርሱ መሣሪያ ነኝ፤” የሚሉት አባ ገብረ መስቀል ተሰማ፣ ቤተ መቅደሱን በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ “ፈቃዱ ከእግዚአብሔር ነው፤ ሃይማኖታዊና አገራዊ ፋይዳ አለው፤ እንደ ሃይማኖታዊነቱ፣ ጥንቱንም የቅዱስ ላሊበላ ቦታ ነው፤ በግራኝ አሕመድ ወረራ ጊዜ ላዩ ጠፍቶ ስለነበር እርሱን ለመመለስ ነው፤” በማለት ያስረዳሉ፡፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ወደ ኢትዮጵያ ከሚመጡ ጎብኚዎች 90 በመቶዎቹ ፍላጎታቸው ላሊበላን መጎብኘት ነው፡፡ በአቅራቢው ሌላ ከአለት የተወቀረና የተፈለፈለ ጥበብ መፈጠሩ፣ ሌላ ዕድል ሌላ ገቢ ይዞ እንደሚመጣ፣ ተጨማሪ በርካታ ቱሪስቶችንም እንደሚስብ ይጠበቃል፡፡
አባ ገብረ መስቀል እስከ አኹን፣ አራት ፍልፍል አብያተ መቅደስን ከወጥ አለት አንፀው ጨርሰዋል፤ ሌሎችንም በማነፅ ላይ ናቸው፡፡ በሥራቸው ግን፣ ዘመናዊ መሣሪያን አይጠቀሙም፤ የምሕንድስና ትምህርትም አያውቁም፤ ግን ሠርተውታል፡፡ እኔ ለማመን እስኪከብደኝ ድረስ ነዉ የገረመኝ ግን እውነት ነው እስኪ እናንተም አይታችሁ ተገረሙ ፡፡
ትክክለኛ ቻናሎች እነዚህ ናቸው
• የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቻናሎች -
? YouTube channel - Subscribe it now, thanks ❤️
namrud pictures & short films -https://youtube.com/channel/UCCW7MBWOARd2N_xupBoJAxw/videos
? የቴሌግራም ቻናላችን- አሁኑኑ join ያድርጉ
@RAFATOEL ZETHIOPIA
(https://t.me/RAFATOEL_ZETHIOPIA)
?የፌስቡክ ገጻችን- አሁኑኑ Follow/Like ያድርጉ
ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ (https://facebook.com/events/542908322957973/)
?በኢንስታግራም አድራሻችን follow
https://www.instagram.com/Rafatoelzethiopia/
?በድረገጻችን
https://rafatoelzethiopia.websites.co.in
ይከተሉን follow,subscribe እና join ያድርጉ እናመሰግናለን
This site was designed with Websites.co.in - Website Builder
We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!
Have a great day!
Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support