ውድ የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቤተሠቦች እንደ ቃላችን
ኢትዮጵያ ሀገሬ ኢትዮጵያ ሀገራችሁ በሐዲስ ኪዳን ይዘን ቀርበናል
መልካም ንባብ!
(((((ሐዲስ ኪዳን)))))
+
17ኛ) የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ በኮከብ እየተመሩ ሄደው የእጅ መንሻ /ገጸበረከት/ ካቀረቡለት (ሰብዐ ሰገል) መካከል የሀበሻው ንጉሥ ባዜን ይገኛል። መድኃኒታችን ሲወለድ መወለዱን በኮኮብ የገለጸላቸው ለእስራኤላዊያን ወይም ለዐረቦች አይደለም። ለሐበሾች እንጅ። ይሄን ክብር ማን አገኘው?
+
18ኛ) ማኅደረ መለኮት እመብርሃን ድንግል ማርያም በስደቷ ጊዜ በሰላም ያረፈችባትና በአስራትነት የተሰጠቻት እንዲሁም በተደጋጋሚ በልጇ መስቀል የባረከቻት ቅድስት ሀገር ቅድስት ምድር
ኢትዮጵያ ነች። ድንግል ሆይ የአስራት ሀገርሽን ኢትዮጵያን አስቢ! አሜን። ይህ ጸሎት ከየት የመጣ ይመስላችኋል? ዘልማዳዊ ነውን? አይደለም!
+
19ኛ) ክርስትናን በጃንደረባዋ አማካኝነት ከዓለም ቀድማ የተቀበለችና መንግስታዊ ሐይማኖት እንዲሆን ያወጀች ሀገር ታላቋ
ኢትዮጵያ ነች። አስተውሉ! ከክርስቶስ ሐዋርያት የአንዱስንኳ ደም ሳይፈስባት በአራቱም ማዕዘናት የወንጌል ብርሀን የበራባት ቅድስት ሀገር ናት ኢትዮጵያ።
+
20ኛ) ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰቀልበትን መስቀል ተሸክሞ ወደ ራስ ቅል ሥፍራ /ቀራኒዮ/ ሲጓዝ መስቀሉን ተቀብሎ በመሸከም ኢየሱስን ያገዘው የቀሬናው ሰው ስምዖን
ሐበሻ / ኢትዮጵያዊ/ ነው። ሮማዊያን ለአይሁድ አሁዶች ደግሞ ለሮማዊያን አሳልፈው ሲሰጡት፣ ወታደሮቹና አለቆቻቸው ያለርኅራሔ ሲገርፉትና ሲያሰቃዩት፣ የእስራኤል ሴቶች ዋይ ዋይ ወዮ ወዮ እያሉ ሲያለቅሱለት፣ የለበሰውን ድርብ በፍታ አውልቀው እጣ ተጣጥለው
ሲወስዱትና ከለሜዳ ሲያለብሱት፣ ሲያፌዙበትና ምራቅ ሲተፉበት፣
ሲገርፉትና ሲያዳፉት፣ የእሾህ አክሊል ሲያጠልቁለት....... ሐበሻው
የቀሬናው ሰው ስምዖን ግን አልጨከነበትም። ኢትዮጵያዊ ሩኅሩህና አዛኝ ነውና። ወዲያዉኑ መስቀሉን ተሸክሞ ነው ያገዘው። ጌታዬን
መስቀሉን ተሸከመለት። ዛሬ ግን መስቀሉን በአንገታችን እንኳን
ልንሸከመው አንወድም። የክርስቶስን መስቀል ወርውረን ማተባችንን
በጥሰን የውሻ ማሰሪያ ሀብል የብረት ሰንሰለት በአንገጣችን አጥልቀናል። በሰንሰለት የታሰርን (በምዕራባዊያን የሴራ ሰንሰለት የታሰርን) ውሾች መሆናችንን በአደባባይ እየመሰከርን ነው። ወዮልን!!!
+
21ኛ) ይህ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል አንድም ነገር ሳይጎድለው ሙሉ መስቀሉ የሚገኘው ግሸን ደብረ ከርቤ /ኢትዮጵያ/ ውስጥ ነው። አስተውሉ! ብዙዎቻችን የምናውቀው ግሼን ማርያም የሚገኘው የመስቀሉ አንደኛው ክፍል እንደሆነ ነው። የምናውቀው አማናዊውን እውነተኛውን መስቀል ዓለም በተለይም የምስራቅ አብያተ ክርስትያናት እንደተከፋፈሉትና ለግብጽ ደርሷት የነበረው የቀኙ ክፍል ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ነው የምናውቀው። ይሄ ውሸት ነው። የመስቀሉ ክፍል ወደ ሀገራችን አልገባም፣ በግሸንም የለም። እዚህ ላይም የግብጽ ጳጳሳት ሴራ አለበት። ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሙሉ መስቀሉ (ጉንደ መስቀሉ) እንጅ ግማሹ (ግማደ መስቀሉ) አይደለም። ግማሹ ቢሆንማ ለንጉሱ ከተገለጸለት ራዕይ ጋር አይጣረስምን? መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አሳርፍ አለ እንጅ የመስቀሌን ጉማጅ (ግማሽ) አላለም። (ለወደፊት አብራራዋለሁ)
+
22ኛ) የአይሁድ ወታደሮች ጎኑን በወጉት ጊዜ እና በቸነከሩት
ጊዜ የፈሰሰውን የክርስቶስን ደም መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በጽዋ
ተቀብሎ ዓለምን ሁሉ ረጨ። ይህ ክቡር ጽዋም ያለው ኢትዮጵያ / ሰሜን ሸዋ/ ውስጥ ነው። ይሄን ምስጢር ጸሀፊ ዓለምአየሁ ዋሴ እሸቴ “እመጓ” በተሰኘው መጽሐፉ ለመዳሰሥ ሞክሯል። እውነት ነው። ያ በእለተ ሀሙስ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ደሙን የሰጠበትና ያ ቅዱስ ዑራኤል አማናዊውን የክርስቶስ ደም ዓለምን የረጨበት ቅዱስና ክቡር ጽዋ የሚገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
+
23ኛ) በዓለም የመጀመሪያው የዜማ ደራሲ ቅዱስ ያሬድ ሐበሻ ነው። እነቬትሆቭንና ሞዛርት ከመወለዳቸው ሽህ አመታት አስቀድሞ የነበረ፣ ዜማን በምልክት ያረቀቀ፣ የዜማ መጽሐፍትን የደረሰ የግዕዝና ዕዝል የአራራይ ስልት ባለቤት ያሬድ ማኅሌታይ፣ ዘሩ ከሊቀ ካህኑ ከሙሴ ወንድም አሮን የሚመዘዘው ያሬድ ኢትዮጵያዊ አይደለምን? እያንዳንዱ ሰው ይሄን እውነት ውስጡ ያውቀዋል። ነገር ግን አምኖ ሊቀበለው አይሻም። ይሄም የራሱ ሴራ አለው።
+
24ኛ) ሦስቱንም ሕጎች ማለትም ሕገ ልቦና፣ ሕገ ኦሪትና ሕገ ወንጌልን የተቀበለች፣ ያስተናገደችና እያስተናገደች ያለች ቅድስት ሀገር እናቴ እምዬ ኢትዮጵያ ነች። የዓለም ሀገራት ክርስትናን
(አምልኮተ እግዚአብሔርን) የተቀበሉት ቀጥታ የባዕድ (ጣዖት) አምልኮታቸውን በመተው ነበር። ሀገሬ ግን አስቀድማ እግዚአብሔርን ስለምታውቀው የእግዚአብሔርን ልጅ እግዚአብሔርን ለመቀበል አልከበዳትም። በዓለም ላይ የሌሉ ጥንታዊያን መጽሐፍት ለምሳሌ፦ መጽሐፈ ሄኖክ፣ መጽሀፈ ኩፋሌ፣ ራዕየ አባ ገሪማ፣ እርገተ ኢሳያስና መጽሐፈ ባሮክ የመሳሰሉት ድንቅ መጽሐፍት የሚገኙት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ከእነዚህ መጽሀፍት መካከል እንደ መጽሐፈ ሄኖክ ያሉት ትክክለኛውን የዓለምን ፍጻሜና የሉሲፈርን ምስጢር ስለያዙ ከምድረ ገጽ እንዲጠፉ
ተደርገዋል። ነገር ግን በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በጥንታዊያን ገዳማት ይገኛሉ። ከእነዚህም በተጨማሪ የሰው ልጅ ያልደረሰባቸው የጥበብ መጽሀፍት እንደሚገኙ ሊቃውንትና ጸሀፍት ይናገራሉ።
............................ እናንተው ጨምሩበት።
ይህችን ሀገር ነው እንግዲህ ተራ የምንላት። ደግሞ የሚገርመኝ
ሀገሪቱን የሚያቃልሏትና የሚያዋርዷት የራሷ ልጆች መሆናቸው ነው። ነጮቹማ ምን ያህል ምስጢራዊ ምድር እንደሆነች ስላወቁ ነው ከጥንት ጀምረው በዐይነ ቁራኛ የሚከታተሏት። በምቀኝነትም
ተነስተው ብዙ ጊዜ ፈትነዋታል። ነገር ግን ኢትዮጵያዬ እንደ ስሟ ወርቅ ናትና በእሳት ተፈትና አልፋለች፣ታልፋለችም። አሁንም በተለያዬ መንገድ እየፈተኗት ይገኛሉ። ሀገሬ ግን ምናልባት ፈተናው ለጊዜው ቢከብዳት እንጅ አትወድቅም። ሀገሬማ በፍጹም አትወድቅም። ብዙ እንቁ ልጆቿ ራሳቸው ወድቀው እርሷን አቁመዋታልና ሀገሬ በጭራሽ አትወድቅም። እናንት የሀገሬን ውድቀትና ሞት የምትመኙ ከንቱዎች!እናንተ የዘመን አተላዎች! እናንተ የእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎች! እናንተ የሉሲፈር ተላላኪ ጭፍራዎች! ሀገሬን የቱንም ያኽል ብትፈትኗትም ግን በጭራሽ አትወድቅም። የቱንም ያኽል የጦር መሣሪያ ይዛችሁ በይፋ ብትገጥሟት፣ ተምዘግዛጊ ሚሳይል ሳይቀር ታጥቃችሁ ብትዘምቱባት በጭራሽ አትሸነፍም። በአንዲት ጸሎት ብቻ ድምጥማጣችሁን ታጠፋችኋለች እንጅ ሀገሬ በፍጹም እጆቿን አትሰጣችሁም። እጆቿ ወደ እግዚአብሔር ነው የተዘረጉት። እናቴ በፈጣሪዋ ሥር ናት። ሽህ ጊዜ ታሪኳን ብትፍቁ ከእኛ ከምንወዳት ልጆቿ ልብ ውስጥ ግን ማውጣት አትችሉም። ምናልባት ጥቂት ባንዳዎችን ማግኘት ትችሉ ይሆናል። ነገር ግን ሐበሻ ሐበሻ ነው። ኢትዮጵያዊ በጭራሽ መልኩን ማንነቱን ሀገሩን ኩራቱን ከቶ አይቀይርም። ሽህ ጊዜ መከራዋን ብታወሩ ሽህ ጊዜ ድሀ ናት ብትሉ የሀገሬን ስም በከንቱ ብትጠሩ ከቶ አይሳካላችሁም። እናቴ ከእናንተ በላይ ሀብታም ነች። ከእናንተ በላይ ባለጸጋ ነች። የሁሉ ነገር ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር አላትና። ዛሬ ምድሯን የከበረ አፈሯን በኬሚካል ብትበክሉት፣ ዛሬ ገበሬው ልጇ እንዳያመርት ብትከለክሉት፣ ድንበሯን አልፋችሁ ባድማዋን ብትወስዱት፣ እኛ ልጆቿ ግን በፍጹም አንራብም። ምግባችንን ለይቶ የሚሰጠን ፈጣሪ አለንና። ዛሬ እኛን ውድ ልጆቿን አንድነታችንን ብታፈራርሱትም እመኑ
ኝ ነገ ይታደሳል። አንድ የምንሆንበት ቀን አይርቅም። ኢትዮጵያ የአድዋን ድል የምኒልክን ድል በእናንተ ላይ ትደግመዋለች። የአድዋ ድል ምስጢር የሆነው ታቦታችንና አንድነታችን ዳግም ይከብራል። እመኑኝ! የድላችን ቀን፣ ዘረኝነትን ቀብረን አንድነትን የምናነግስበት ያ ቀን ቅርብ ነው። በተባበረ ክንዳችን ሀገራችንን ወደ ቀደመ ክብሯ የምንመልስበት ቀን ደርሷል። የሀገራችን የኢትዮጵያችን ትንሣኤ ደርሷል። ያን ጊዜም እናንተ ዛሬ ሀገሬን፣ የማንነቴን መገለጫ ኩራቴን፣ እምዬ ኢትዮጵያን የናቃችሁ የውስጥና የውጭ ጠላቶቿ ሁሉ አንገታችሁን ትደፋላችሁ። ወደ እግሯ ጫማም ትሰግዳላችሁ። እናቴን ማሪኝ ትሏታላችሁ። የፋቃችሁት፣ ያጠፋችሁትና የበረዛችሁት ታሪኳ ይስተካከላል። አንድ ቀን ሁሉም መልካም ይሆናል። ኢትዮጵያዬ ሆይ! የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ መቀነትሽ ከፍ ይላል። አርማሽ በክብር የአርያም ደጃፍ ይደርሳል።
ከፍታሽ ቀርቧልና ተነሺ!።
እግዚአብሔር ሆይ! ኢትዮጵያዬን ባርክ። አሜን!!!
ትክክለኛ ቻናሎች እነዚህ ናቸው
• የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቻናሎች -
? YouTube channel - Subscribe it now, thanks ❤️
namrud pictures & short films -https://youtube.com/channel/UCCW7MBWOARd2N_xupBoJAxw/videos
? የቴሌግራም ቻናላችን- አሁኑኑ join ያድርጉ
@RAFATOEL ZETHIOPIA
(https://t.me/RAFATOEL_ZETHIOPIA)
?የፌስቡክ ገጻችን- አሁኑኑ Follow/Like ያድርጉ
ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ (https://facebook.com/events/542908322957973/)
?በኢንስታግራም አድራሻችን follow
Rafatoelzethiopia
?በድረገጻችን
https://rafatoelzethiopia.websites.co.in
ይከተሉን subscribe እና join ያድርጉ እናመሰግናለን
This site was designed with Websites.co.in - Website Builder
We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!
Have a great day!
Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support