ሰላም የራፋቶኤል ቤተሰቦች አነሆ በጥያቄያችሁ መሠረት ስለ ቆ በትር ጥቂት ልንላችሁ ወደድን መልካም ቆይታ
ፈጣሪ በስድስቱ ቀናት ውስጥ ከፈጠራቸው አሰደናቂና አስገራሚ ፍጥረታት አንዱ ቆ በትር ነው ስንቶቻችን ስለ ቆ በትር እናውቃለን?
ቆ በትር በስድስተኛው ቀን እንደተፈጠረችና ለአዳም እንደተሰጠችው በጣና ገዳማት ውስጥ የሚገኙ ጥንታዊ መፅሀፍት ያትታሉ የተለያዩ የ ቆ በትር ጠልሰሞችም በገዳሙ ውስጥ ይገኛሉ።
ይህ ቆ የእግዚአብሔር የከበረ ስም እንደሆነም አባቶች ይናገራሉ ይህም ብቻ አይደል ከቶ መስቀል በራሱ ቆ በትር ትበልጣለች ይላሉ ለዚህም ምንጩ መፅሀፈ ሄኖክ ይሆናል።
ቆ በስድርተኛው ቀን እንደተፈጠራችና ለአዳም የተፈጠረች ልዩ ሀይል ያላት መለኮታዊ በትር እይደሆነች በብዙዎች ዘንድ የታመነ ነው ይህንንም ለማለት ግድ የሚሆነው የቆን ታሪክ ስንመለከት ነው።
እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው
ዘፍጥረት 1 (Genesis)
27፤ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
28፤ እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ "ግዙአቸው።"
ብሎ የምድር ሁሉ ገዚ ጌታ አድርጎ ሲፈጥረው አዳም ሁሉ እንዲገዛለት ሀይል የሆነችው ይቺ የንግስናው ቆ በትር ናት።
ኖኅ በምድር ሁሉ ላይ ሀጥያት በበዛ ጊዜ እግዚአብሔርም ሰውን በመፈጠሩ ተፀፀተ እስኪል መፅሀፍ የሰው ልጅ በደል በበዛች ጊዜ በምድርም ላይ የንፍር ውሀ ሲዘጋጅላት ኖኅ ይቺን በትር በመያዙ የኖኆ መርከብ ከንፍር ውሀ ለመትረፍ ችላለች። እዚጋ ፣አፅንኦት ልንመለከተው የሚገባው ነገር ሲዘንብ የነበረውን የንፍር ውሀ እንኳን በዛ ዘመን የተሰራች መርከብ አሁን እጅግ በመጠቀ ቴክኖሎጂ የሚሰሩት መርገቦች ሊቋቋሙት አይችሉም ነበረ። ይህም ብቻ አደለም በአለማችን ላይ ብዙ አይነት ዝርያ ያላቸው እንሰሶች አሉ እነዚያን ሁሉ እንሰሶች እንዴት አንዲት መርከብ ትችላቸዋለች? ያውም በዚያ ዘመናዊ መርክብ በሌለበት ዘመን። ነገር ግን አባቶች ሁሉን እንዲችል ያደረገችው ይቺ ቆ በትር ናት ይሉናል መርከቢቷን ያፀናቻት ያስቻለቻትም ይቺ በትር ናት።
እግዚአብሔር ለኖኅ እንዲህ አለው
ዘፍጥረት 6 (Genesis)
13፤ እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፦ የሥጋ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል፤ ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተሞልታለችና፤ እኔም እነሆ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ።
14፤ ከጎፈር እንጨት መርከብን ለአንተ ሥራ፤ በመርከቢቱም ጉርጆችን አድርግ፥ በውስጥም በውጭም በቅጥራን ለቅልቃት።
15፤ እርስዋንም እንዲህ ታደርጋታለህ፤ የመርከቢቱ ርዝመት ሦስት መቶ ክንድ፥ ወርድዋ አምሳ ክንድ፥ ከፍታዋ ሠላሳ ክንድ ይሁን።
16፤ ለመርከቢቱም መስኮትን ታደርጋለህ፤ ከቁመትዋም ክንድ ሙሉ ትተህ ጨርሳት፤ የመርከቢቱንም በር በጎንዋ አድርግ፤ ታችኛውንም ሁለተኛውንም ሦስተኛውንም ደርብ ታደርግላታለህ።
17፤ እኔም እነሆ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።
18፤ ቃል ኪዳኔንም ከአንተ ጋር አቆማለሁ፤ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ።
19፤ ከአንተ ጋር በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሥጋ ካለው ከሕያው ሁሉ ሁለት ሁለት እያደረግህ ወደ መርከብ ታገባለህ፤ ተባትና እንስት ይሁን።
20፤ ከወፍ እንደ ወገኑ፥ ከእንስሳም እንደ ወገኑ፥ ከምድር ተንቀሳቃሽም ሁሉ እንደ ወገኑ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይግቡ።
ይህን ቃል ተመልክተን ሄኖክ ደግሞ ቃሉን ሲያፀናልን እንዲህ አለ
"እግዚአብሔር ተናገረ ወደ ላሜህ ልጅ ወደ ኖኅም አርሰየላልዩርን ላከው እንዲህም በለው አለው ? በእኔ ስም ራስህን ሰውር(አድን) ምድር ሁሉ ትጠፋለችና ? ሄኖክ ፫÷፩-፪
ከላይ ሄኖክ የፃፈው እግዚአብሔር ለኖኅ እራስህን በእኔ ስም ሰውር ውይም አድን ያለው ወይም እግዚአብሔር ስም ብሎ የጠራት ይቺ ቆ በትር እንደሆነች በመግለፅ ቆ የእግዚአብሔር የከበረ ስም መኆኗንም አባቶች የናገራሉ።
ይች ቆ በትር ስትወራረስ መጥታ ሙሴ ኤርታራን ባህር የከፈለባት እንዲሁም ከሱ በፊት የዮቶር የጥበብ ምንጭ ሆና የነበረችው ይች በትርም እንደሆነች እና ሙሴም ከዮቶር ብልሀትን ጥበብን ሲማር ከሱ የወረሳት እንደሆነች አባቶች ይናገራሉ ስለ ቆ በትር በጥልቀት ያጠኑት እነ ሀኪም አበበች በስፋት ይናገራሉ። ዮቶር ደግሞ ኢትዮጵያዊ መሆኑ አጀብ ያስብላል።
ዘጸአት 4
2፤ እግዚአብሔርም፦ ይህች በእጅህ ያለችው ምንድር ናት? አለው። እርሱም፦ በትር ናት፡ አለ።
ዘጸአት 4
17፤ ይህችንም ተአምራት የምታደርግባትን በትር በእጅህ ይዘሃት ሂድ።
ሙሴም በመፅሀፍ ቅዱር በተፃፈው መሠረት ብዙ ገቢረ ተአምራትን ፈፅሞባታል በፈርኦን ላይ አምላክ ተደርጎ በእግዚአብሔር እስኪሾም ድረስ ብዙ ተአምራትን ፈፅሞባታል
ዘጸአት 14 (Exodus)
16፤ አንተም በትርህን አንሣ፥ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ፥ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ።
ዘጸአት 14 (Exodus)
21፤ ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የምሥራቅ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፥ ባሕሩንም አደረቀው፥ ውኃውም ተከፈለ።
22፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ መካከል በየብስ ገቡ፤ ውኃውም በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ሆነላቸው።
እነዚህንና ሌሎችም ተአምራትን በበትሯ አድርጓል ሙሉ ምዕራፉን ማንበብ ከበቂ በላይ ነው። ታድያ ይች በትር ከሙሴ በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው በንግስት ኢተያ ዘመን እንደሆነ ታሪክ ይናገራል። አባቶችም ይቺ በትርን በጣና ሀይቅ ካሉት ገዳማት በአንዱ እንዳለች ይናገራሉ። እነ ሀኪም አበበችን የመሰሉ ሲፊ ጥናት ያኪያሄዱ አጥኚዎች ደግሞ በጣና ሀይቅ ውስጥ እንዳለች ይናገራሉ ይህንንም ሲያስረዱ ኢተያ በታንኳ ጣናን ስታቋርጥ በባዕዳን ስለተከበበች ከነሱ ቅርሶችን ለማትረፍ ታንኳዋን እንዳሰመጠቻትና እራሷን እንዳጠፋች ቆ በትርንም ይዛት እንደሰመጠች የናገራሉ።
ስለ ቆ በትር ለዛሬ ያዘጋጀነው ይህን ይመስላል በሌላ ጊዜ በሌላ ርዕስ ስለ ጥንታውያን የምናውራ ይሆናል እስከዛው ሰናን ሶቤ።
Show on YouTube ቆ በትር " https://youtu.be/VeRr5lTqVXM "
ይቆየን!!!
መልካም ዕለተ ሠኑይ
***********************************
ትክክለኛ ቻናሎች እነዚህ ናቸው
????????
• የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቻናሎች -
? YouTube channel - Subscribe it now, thanks ❤️
namrud pictures & short films -https://youtube.com/channel/UCCW7MBWOARd2N_xupBoJAxw/videos
? የቴሌግራም ቻናላችን- አሁኑኑ join ያድርጉ
@RAFATOEL ZETHIOPIA
(https://t.me/RAFATOEL_ZETHIOPIA)
?የፌስቡክ ገጻችን- አሁኑኑ Follow/Like ያድርጉ
ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ (https://m.facebook.com/%E1%88%AB%E1%8D%8B%E1%89%B6%E1%8A%A4%E1%88%8D-%E1%8B%98%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-112582176799540/?tsid=0.7487612614507868&source=result)
?በኢንስታግራም አድራሻችን follow
https://www.instagram.com/Rafatoelzethiopia/
?በድረገጻችን
https://rafatoelzethiopia.websites.co.in
Follow, subscribe እና join ያድርጉ እናመሰግናለን
??????????
This site was designed with Websites.co.in - Website Builder
We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!
Have a great day!
Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support