X

By ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ
Tue, 26-Nov-2019, 14:46

ደቂቀ ሴት፣መላዕክት ወብሔረ ህያዋን

ሰላም የራፋቶኤል ቤተሰቦች ዛሬ ደግሞ ልንነግራችሁ  የወደድነው ስለ ደቂቀ ሴት፣መላዕክት ወብሔረ ሕያዋን ነው።

በጥያቄው ለተሣተፋችሁ ሁሉ እናመሰግናለን።

መልካም ቆይታ

ደቂቀ ሴት፣መላዕክት ወብሔረ ህያዋን 
                  ደቂቀ ሴት
 እነዚህ በደብረ ቅዱስ ተለይተው  እግዚአብሔርን እያመሠገኑ ይኖሩ የነበረ ሲሆን በባህሪያቸው ሰው ስለሆኑ ከሰው ልጆች ጋር በተፈጦሮአዊ መንገድ መዋለድ የሚችሉ ናቸው።
                መላዕክት 
እነዚህ ደግሞ እንደየ ነገዳቸው እንደየስልጣናቸው በላይ በሰማይ እግዚአብሔርን ያለ እረፍት እያመሠገኑ የሚኖሩ ሲሆኑ በባህሪያቸው ፆታ የሌላቸው ሲሆኑ ወንድ ወይም ሴት ብለን ልንሰይማቸው አንችልም ስለዚህም መላዕክት በሰዋዊ ተፈጥሮ ስርአት ከሰው ልጅ ጋር መጋባትም ሆነ መዋለድ አይችሉም ምክንያቱም ከባህሪያቸው ጋር ስለማይስማማ።
            ብሔረ ሕያዋን
እነዚህም ደግሞ  በተመሳሳይ ሰዎች ሲሆኑ ነገር ግን ሳይሞቱ በሕይወት እያሉ  የተነጠቁ ናቸው ለምሳሌ ኤልያስ በሰረገለ መነጠቅና ሄኖክ የፈአቡነ አረጋዊ የመሳሰሉት ወደዚህ ቦታ የተነጠቁ ናቸው። በባህሪያቸው የሰው ልጆች ስለሆኑ መውለድ መዋለድ የሚችሉ ቢሆንም ከተነጠቁ በኋላ ግን ከሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ይቆምና እንደ መላዕክት ይኖራሉ። 

ሰላም የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቤተሰቦች እንዴት አረፈዳችሁ የጥያቄውን ማብራሪያ ሚዛናዊና ገለልተኛ በሆነ መንገድ ለማቅረብ ተገደናል ይህም የሆነበት ምክንያት ሶስቱም አሳማኝ ሀሳቦች ስለሚቀርብባቸው ነው። መልካም ንባብ

           ደቂቀ ሴት
ደቂቀ ሴት ናቸው እንጂ መላዕክት አደሉም ብለው ሀሳብ የሚያቀርቡ ሰዎች ማስረጃ አድርገው የሚያቀርቡት ከላይ እንደጠቀስነው መላዕክት በራሳቸው ፆታ የሌላቸው መሆኑ በባህሪያቸውም ማግባት መጋባት መውለድ መዋለድ የማይስማማቸው መሆኑን በመጥቀስ ከሰው ልጆች ጋር ተጋብተው ኔፍሌም እንዲወለዱ ምክንያት የነበሩት በደብረ ቅዱስ ይኖሩ የነበሩት ሁለት መቶ የሴት ልጆች  ናቸው ኔፍሌም የመላዕክት ውላጅ ናቸው የሚለው አስተምህሮን ያመጡት የኔፍሌም ዝርያ አሁንም ድረስ ስላለና እኛ የሀጢያተኛው የአዳም ዘር አደለንም የመላዕክት ዘር ነን ለማለት ነው። በማለት ሀሳባቸውን ይሞግታሉ። 

            መላዕክት
ይህንን ሀሳብ ደግፈው የሚከራከሩት ደግም ኔፍልም ሰው ከሰማይ መላዕክት ጋር ተጋብቶ የወለዳቸው ልዩ ፍጡራን ናቸው ብለው በሙሉ እምነት ያምናሉ። የተለያዩ ገደላትንና ብራናንም ይገልጣሉ አንዳንድ ጥንታዊ መፃሕፍትም መላዕክት የሰውን ልጆች ሀጥያት ተመልክተው እርስ በርስ በሰው ልጆች ላይ ተናደው አወሩ (አሙት) እግዚአብሔርም ስለምን በመልኬ የሰራሁትን የሰው ልጅ ላይ እርስ በርስ አወራችሁባቸው  ብሎ ጠየቃቸው እነሱም ሁሉን ነገር አብልጠህ ሰጠኸው ከፍጠራታት ሁሉ ከእኛም በላይ ክቡር አረከው ግን እሱ አንተን ከዳህ በማለት ለእግዚአብሔር መልስ እንደሰጡና እግዚአብሔርም  እናንተስ መላዕክት ሰለሆናችሁ ይህን አሰባችሁ እንጂ ሰው ብትሆኑ እናንተም በከዳችሁኝ ነበረ አላቸው እነሱም ጌታ ሆይ እኛ የሰውን ልጅን ብንሆንስ ባከበርንህ ነበረ እንጂ አንከዳህም ነበረ ይህን ማረጋገጥ ከፈለክ ፈትነን በማለት ከእግዚአብሔር ጋር ንግግር እንዳደረጉ እና በመጨረሻም እግዚአብሔር ሊፈትናቸው ፍፁም ሰው አድርጎ ሁለት መቶ መላዕክትን እንደላካቸውና በመጨረሻም መፅሐፍ ሄኖክ ላይ የተፃፈው ታሪክ እንደተፈፀም ከሰው ልጆች ጋር እንደተኙና ኔፍሌም እንደተወለዱ መላዕክት ናቸው ብለው የሚያምኑት ሀሳባቸውን መፅሀፍትን በመጥቀስ ያቀርባሉ።

             ብሔረ ሕያዋን 
ይህን ሀሳብ የሚያራምዱ ደግሞ ከሰው ልጅ ጋር ተዋልደው ኔፍልምን እንዲፈጠሩ ምክንያት የሆኑት በብሔረ ሕያዋን ይኖሩ የነበሩት ሰዎች እንደሆኑ እስረግጠው ይናገራሉ።የሰው ልጅ በብሔረ ሕያዋን እንደመላዕክት እያመሠገነና እያመለከ ስለሚኖር አኗኗሩ እንደ ምንኩስና ነው ስለዚህም ከሰው ልጅ ጋር መጋባት ለነሱ አይፈቀድም ነገር ግን በብሔረ ሕያዋን ከሚኖሩት ሁለት መቶዎቹ እግዚአብሔርን ክደው በሰውል ሴት ልጆች ተማርከው እንደተኙና በዚህም የቁጣ ልጅን እንደወለዱ ይናገራሉ። ደቁቀ ሴት ናቸው የሚለውን አስተምህሮንም የሴት ልጆች የሚኖሩት በምድር ላይ ነው በምድር ሳሉ እንዳያገቡ የሚከለክላቸው ሕግ የለም ስለዚህ ቢጋቡ የቁጣ ልጅ የሚወልዱበት ምክንያት የለም በማለት የሞግታሉ።

ውድ የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቤተሰቦች ከላይ የተዘረዘሩትን ስንመለከት ሁሉም በራሳቸው መንገድ አሳማኝ ናቸው ነገር ግን ከሶስቱ በአንዱ መንገድ ኔፍሌሞች ተወልደዋል። በቀጣይ ክፍል ሰፋ ባለ በዚሁ ርዕስ ተመልሰን እንመጣለን እስከዛው መልካም ጊዜ።
ይቆየን!!!
 መልካም ዕለተ ሠኑይ
***********************************
ትክክለኛ ቻናሎች እነዚህ ናቸው
????????
• የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቻናሎች - 
? YouTube channel - Subscribe it now, thanks ❤️
namrud pictures & short films -https://youtube.com/channel/UCCW7MBWOARd2N_xupBoJAxw/videos
? የቴሌግራም ቻናላችን- አሁኑኑ join ያድርጉ 
@RAFATOEL_ZETHIOPIA
(https://t.me/RAFATOEL_ZETHIOPIA)
?የፌስቡክ ገጻችን- አሁኑኑ Follow/Like  ያድርጉ 
ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ (https://m.facebook.com/%E1%88%AB%E1%8D%8B%E1%89%B6%E1%8A%A4%E1%88%8D-%E1%8B%98%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-112582176799540/?tsid=0.7487612614507868&source=result)
?በኢንስታግራም አድራሻችን follow 
https://www.instagram.com/Rafatoelzethiopia/
?በድረገጻችን 
https://rafatoelzethiopia.websites.co.in
Follow, subscribe እና join ያድርጉ እናመሰግናለን
??????????

ሀሳብ አስተያየታችሁን
????????
 @Rafatoel_bot     
r*****************@g*****.com
????????

This site was designed with Websites.co.in - Website Builder

WhatsApp Google Map

Safety and Abuse Reporting

Thanks for being awesome!

We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!

Have a great day!

Are you sure you want to report abuse against this website?

Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support