X

By ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ
Sun, 24-Nov-2019, 20:03

ሰዉና ወፍን የሚያዋልደዉ ተአምረኛዉ ድንጋይ

ሰላም ሰላም እንደምን አመሻችሁ 

 ሰዉና ወፍን ስለሚያዋልደዉ ተአምረኛዉ ድንጋይ እነናያለን፡፡

 ድምፁ እንደ ብረት የሚጮህ፤ እንደመስታዉት የመሰለ ፤እንደ እንቁ የሚያበራ፤ ናብሊስ የሚባል ድንጋይ አለ፡፡ መልኩም እብነ በረድን ይመስላል፡፡ የታመመ ሰዉ ጭንቅ ሲበዛበት እና ነፍሱ አልወጣ ካለች ይህንን ድንጋይ በጀሮዉ  አጠገብ የመቱለት እንደሆን ያለ ጭንቀት ነፈስ ከስጋ በቀላሉ ትለያለች ፃይርም አይኖረዉም፡፡


  እንዲሁም  በምጥ የተያዘችና የተጨነቀች ሴት  እሱን ስትነካ በፈጥነት ትወልዳለች፡፡

ወፍም ስትታመም እና ፃይር ሲበዛባት ከዚህዉ ታምረኛ ድንጋይ ላይ በመቀመጥ እፎይታን ታገኛለች፡፡ 

ይህንን እና ከዚህ ቀደም ከዚህዉ የቴሌግራም  ፔጀ ላይ እንደፃፍኩት ብዛት ያላቸዉ ማእድናት

የሚሰጡት አገልግሎት ዘርፈ ብዙ መሆኑ ነው። ምእራቡ አለም sound therapy እና crystal Therapy ብሎ የሚሰጠውን  ህክምና አያቶቻችን ከሺህ ዘመናት

አስቀድሞ አገልግሎት ይሰጡበት ነበር። በተለይም ናብሊስ እና #ያክንት የተሰኙት ማእድናት ከህክምና ጋር ተያይዞ በርካታ የፈውስ አገልግሎቶችን ይሰጡ ነበር።

ኢያሰጲድ እና ብርቄ የተሰኙት ማእድናት ደግሞ የፀሐይ ብርሃን በማመቅ ብርሃን መልሰው የሚያንፀባርቁ ልክ እንደ ዳይመንድ ውብ እና ጠንካራ ማእድናት ናቸው።

ብርቄ እና ናብሊስ የተሰኙት ማእድናት ድምፅን አምቀው በመያዝ መልሰው የማንፀባረቅ አገልግሎትም ይሰጣሉ።

ቅድስ ላልይበላ እና የየምርሐነ ክርስቶስ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ ብርቄ እና ናብሊስ የተሰኙት ማእድናት በውስጥ የቤተክርስትያኖቹ ግንባታ ጋር ተጣምረው ተሰርተው ነበር ይህም የሆነው ብርሀን እና ድምፅን መልሰው እንዲያንፀባርቁ ለማድረግ ነበር። 

በምስጢር ማህበረሰቡ ለዘመናት እየታሰሱ ካሉ ጥንታዊ ቅርሶች መካከል አስራ ሁለቱ ሚስጢራዊ ማእድናት ናቸው እኒህን 12 ከዚህ ቀደም ለመግለፅ ሞክሬያለሁ ለማስታወስ ወደ ኀላ  ይዶ ማንበብ ይቻላል። እነህ አስራ ሁለት ማእድናት ለካህኑ አሮን

የተሰጡት ናቸው [ ዘፀ 28)። እነኚህ ማእድናት እስካሁን በይፋ ያልተደረሰባቸው ልዩ ምስጢራት እንዳላቸው ይነገራል። ከነህ አስራ ሁለት ማእድናት መካከል አስራ

አንድ በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ እንደሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። እነኚህ አስራሁለቱ የከበሩ ማእድናት:

ኢያሰጲድ፣ያክንት፣ሰንፔር፣ኬክቄዶን፣መረግድ፣ሰርዶንክስ...

እና አማቴስጢኖስ ይሰኛሉ (ራዕ 21:29) ። ከነኚህ ማእድናት አንዳንዶቹ ለትላልቅ የኤሌክትሮኒክስና የቴክኖሎጂ ምርቶች የሚፈለጉ ናቸው። 

  አሁን ላይ እኒህ የከበሩ ድንጋይ በምዕራባዉያን የከረሰ ምድር አጥኝወች ተገቢወን በጀት ተበጅቶለት በኢትዮጵያ ምድር ላይ  በፍለጋ በሰፊዉ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡

የዚህ ፅሁፍ ዋና አላማዉ እኛስ ለምን የሀገሬን ሰረዶ በሀገሬ በሬ እንዲሉ የኛ የሆኑትን ለኛዉ ለማድረግ አንረባረብም ነዉ፡፡

ነገር ግን የዚህ የከበር ድንጋይ መገኛዉ የት ይሆን?? እንዳለ እናምናለን ግን የት ነዉ መገኛዉ ነዉ ጥያቄዉ.........የአባይ ሸለቆ ዉስጥ ይሆን ????

ይህንን ፈለጎ የማገኝት ሀላፊነት አለብንን።

ትክክለኛ ቻናሎች እነዚህ ናቸው

• የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቻናሎች - 

? YouTube channel - Subscribe it now, thanks ❤️

namrud pictures & short films -https://youtube.com/channel/UCCW7MBWOARd2N_xupBoJAxw/videos

? የቴሌግራም ቻናላችን- አሁኑኑ join ያድርጉ 

@RAFATOEL ZETHIOPIA

(https://t.me/RAFATOEL_ZETHIOPIA)

?የፌስቡክ ገጻችን- አሁኑኑ Follow/Like  ያድርጉ 

ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ (https://facebook.com/events/542908322957973/)

?በኢንስታግራም አድራሻችን follow 

https://www.instagram.com/Rafatoelzethiopia/

?በድረገጻችን 

https://rafatoelzethiopia.websites.co.in

ይከተሉን subscribe እና join ያድርጉ እናመሰግናለን፡

This site was designed with Websites.co.in - Website Builder

WhatsApp Google Map

Safety and Abuse Reporting

Thanks for being awesome!

We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!

Have a great day!

Are you sure you want to report abuse against this website?

Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support