X

By ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ
Mon, 25-Nov-2019, 03:22

"የግእዝ ቋንቋ ምንነት"

ውድ የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ?

ሠላመ እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ይሁን አሜን።

ዛሬ ትንሽም ቢሆን  "የግእዝ ቋንቋ ምንነት" በሚል ጥቂት ልንላችሁ ወደድን መልካም ቆይታ

በመፃህፍ ቅዱስ ላይ  ዘፍ ፲፩÷፩ (11-1)

እንዲህ ይላል 

 "ወአሀዱ ነገር ለኩሉ ዓለም ወአሀዱ ቃሉ"

የሰዉ ሁሉ ቋንቋዉ አነጋገሩም አንድ ነበር ይላል፡፡ ስለዚህ ጥያቄ የሚሆነዉ ...

ሰዉ ከፈጣሪዉ ጋ የሚግባባበት ሰማያዊዉ የእዜር  ድርሰት የሆነዉ ቋንቋ የቱ ቋንቋ ነዉ?


 እንግዲህ ይህ ሰማያዊዉ ቋንቋ በሰዉ ልጆች ዘንድ ለዘመናት እንደተነገር እና አሁንም እየተነገረ መሆኑ እሙን ነዉ፡፡

ቅዱስ መፃህፍ እንደሚያስረዳን የሰዉ ልጂ የቋንቋ አንድነቱ ከአዳም አባታችን አልፎ ፤ ከጥፋት ዘመን ተሻግሮ፤ ሶስቱ የኖህ ልጆችና ሚስቶቻቸዉ ጋር ማይ አይህን ተሻግሮ፤ የኖህ ዘሮች በምድር ላይ  በዝተዉ በስናኦር ምድር ላይ የባቢሎንን ግንብ እስኪ ገነቡ ድረስ የሰዉ ልጂ ቋንቋ አንድ ነበር  ዘፍ 11:1 ፡፡ 


ታድያ ያ ቋንቋ ማን ነዉ...??


ይህ ምስጥራዊ የሆነዉ  ሰማያዊ ወምድራዊ ቋንቋ ግእዝ ነዉ፡፡

ግእዝ የመጀመሪያው የአለም ቋንቋ እንደሆነ ጥቂት የማይባሉ ምሁራን በማስረጃ ይናገራሉ።  ለመሆኑ ማስረጃወች ምንድን ናቸዉ....

 ማስረጃ 1


    በአለም ላይ ተፅኖ ፈጣሪ ዘመን ተሻጋሪ በቀደምትነቱም በጥንታዊነቱ እጂግ የቀደመ ተወዳዳሪም ያልተገኘለት ታላቁ መፃህፍ ነጮች  book of life በማለት ትልቅ ክብር የሚሰጡት መፅሀፈ ሄኖክ በፅሁፍ የተገኘው በግእዝ ብቻ ነው። 

  እዚህ ላይ ልብ በሉልኝ ቤተሰቦቸ ሄኖክ የያሬድ ልጂ የማቱሳላም አባት እንዲሁም የአዳም 7 ኛ ትዉልድ ሲሆን   ከሙሴ ሺህ አመታት በፊት ነበር ዘፍ 5:21 ። የዚህም ታላቅ የግዜር ወዳጂ የሆነዉ የሔኖክ መፃህፎቹ የተገኙት በግእዝ ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደሆን በሁሉም የአለም ህዝብ የታመነና የተረጋገጠ ነዉ፡፡

 ይህ ደግሞ የአዳም 7ኛ ትዉልድ ሔኖክም ቋንቋዉ ግእዝ ነበር ለማለት ያስችላል፡፡

ለምን በሌሎች ቀደምት በሚባሉት ቆንቋወች አልተገኘም??

ለምን በእብራይስጥ አልተገኘም አልተፃፈም? ?ለምንስ በአረማይክ አልተከተበም ?



ማስረጃ 2

አዳም የሚለዉ የሰሙ ትረጉም በየትኛዉ የአለም ቋንቋ ትርጉም አይገኝለትም ፡፡

ነገር ግን አዳም ብሎ ፈጣሪ ስሙን የሰየመዉ   በግእዝ ትርጉም ሲኖረዉ እናያለን ትርጉሙም የአማረ የተዋበ ማለት ነዉ፡፡

ለምን በሌሎች ቋንቋ  አዳም የሚለዉ ፈጣሪ የሰየመዉ የስሙ ትርጉም አልኖረዉም ?


ማስረጃ 3

በመላዉ አለም ያሉት ሁሉም የሰወች  ቋንቋወችና ፊደሎቻቸዉ በተናጋሪወቻቸዉ ህዝቦች ወይም ጎሳወቻቸዉ ሲጠሩ  ለምሳሌ የእንግሊዞች እንግሊዘኛ የፈረንሳይ ፍሬች ...ግእዝ ግን በራሱ ስም ብቻ ነዉ የሚጠራዉ::


ማስረጃ 4

የግእዝ ፊደሎች መደበኞች የሆኑት 22 አሌፋት ናቸዉ እነዚህም በ6 ቀን ከተፈጠረት 22 ስነ ፍጥረታት ጋር በቁጥር መመሳሰላቸዉ ና እያንዳንዳቸዉ አሌፋት የእግዜር የመታወቂያ ስሞች ከመሆናቸዉ ባሻገር በስያሜ በመልክና በድምፅ ይዘታቸዉ ከተቀናጁት ከመለኮታዊ ሃይል 7 ቁጥር ጋር ባላቸዉ ሚስጥራዊ ግንኙነት ነዉ ፡፡

ለምሳሌ ግእዙ ወይም የመጀመሪያዉ ሆሄ የዉስጥ ተነባቢ በ "ኧ " ጀምረዉ ሳብዕ ወይም ሰባተኛዉ ሆሄ በ "ኦ" የሚፈፀሙ መሆናቸዉ፡፡

ለምሳሌ" መ" ሲነበብ " ኧ "የሚል ወስጣዊ ተነባቢ አለዉ እንዲሁም  ሰባተኛዉን "ሞ" ብንወስድ  " ኦ" የሚል ዉስጣዊ ተነባቢ እናገኛለን፡፡ 

ታዲያ ይህ መሆኑ ከምን አምላካዊ ሚስጥር ጋ ያገናኘዋል ያልን እንደሆን ?

  "አነ ዉእቱ አልፋ ወኦ አነ ቀዳማዊ ወአነ ዳሀራዊ ርዕዝ ወማኃልቅት"


በቃልነቴ ለማንነቴ መገለጫ መነሻ እንደሆነዉ ሁሉ "ኧ" እና መዳረሻዉ እንደሆነዉ እንደ " ኦ" አሌፋት እኔ ፊተኛዉና ኀለኛዉ መጀመሪያዉና መጨረሻዉ እኔ ነኝ ብሎ በዮሐንስ ራዕይ 22: 13 እንደገለፀዉ፡፡


ማስረጃ 5


 ማስረጃ 6

:

:

:

 ለአብነት ያክል ይህንን ማስረጃ አቀረብኩላችሁ እንጂ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ 

ለዚህም ነዉ ብዙ ነጮች አሁን ላይ የግእዝን ታላቅነት ተረድተዉ እሰከ phd ድረስ በየ ኮሌጆቻቸዉ የሚሰጡት፡፡


ዋቢ 

1) ከየኔታ ወንበር

2) መፃህፍ ቅዱስ ፪ሽ እትም

3)አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት መፃህፍ

4)wikipedia the origin of Geez

አበቃሁ መልካም ዕለተ ሠኑይ

***********************************

ትክክለኛ ቻናሎች እነዚህ ናቸው

• የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቻናሎች - 

? YouTube channel - Subscribe it now, thanks ❤️

namrud pictures & short films -https://youtube.com/channel/UCCW7MBWOARd2N_xupBoJAxw/videos

? የቴሌግራም ቻናላችን- አሁኑኑ join ያድርጉ 

@RAFATOEL ZETHIOPIA

(https://t.me/RAFATOEL_ZETHIOPIA)

?የፌስቡክ ገጻችን- አሁኑኑ Follow/Like  ያድርጉ 

ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ (https://facebook.com/events/542908322957973/)

?በኢንስታግራም አድራሻችን follow 

https://www.instagram.com/Rafatoelzethiopia/

?በድረገጻችን 

https://rafatoelzethiopia.websites.co.in

ይከተሉን subscribe እና join ያድርጉ እናመሰግናለን

This site was designed with Websites.co.in - Website Builder

WhatsApp Google Map

Safety and Abuse Reporting

Thanks for being awesome!

We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!

Have a great day!

Are you sure you want to report abuse against this website?

Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support