X

By ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ
Sun, 24-Nov-2019, 08:22

የተ ቤቶች ትርጓሜ

ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ

***********

ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ  ትርጉም እንመለከታለን። በግዕዝ ቋንቋ መሰረት የተ ፊደል ዘሮች ጠልሰማዊና ፊደላዊ ፍች አላቸው። ፍቻቸውም ምድራዊ ብቻ ሳይሆን ሰማያዊም ጭምር ነው::

1ኛ) ጠልሰማዊ ፍች፦

ተ ማለት ምዕራብ ምስራቅ ሰሜን ደቡብ፣ ቅርፀ አዳም፣ ማዕከላዊ: መስቀል: በሁሉ ላይ የተሾመ ማለት ነው::

ቱ ማለት "አዳም ብቻውን እንዳይሆን ከግራ ጎኑ ሰው እንፍጠርለት" ማለትን ያመለክታል:: ከአንድ ሁለት መሆንን ያሳያል::

ቲ ማለት ዲያቢሎስ በቀኝ የነበረውን አዳም በግራ ሊያደርገው መንቀሳቀሱን ማለትም የሄዋንን መሳሳት የሚጠቁም ነው::

ታ ማለት የአዳም እና የሄዋን በሰሩት ሃጢያት መፀፀትና ወደ ፈጣሪያቸው መመልከታቸውን: ከግራ ወደ ቀኝ እንዲመልሳቸው መማፀናቸውን ያሳያል::

ቴ ጠልሰም እጅግ ትልቅ ሚስጥርን የያዘ ነው:: ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በሲኦል በዳቢሎስ ቀንበር ሲማቅቅ የነበረን ነፍስ ሁሉ ለማዳን 'ቴ' ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሲኦል መውረዱን የሚያመላክት ነው:: ይህ 'ቴ' በተዓምረ ኡራኤል ላይ የሚነበብ ነው:: ይህ ጠልሰም ጌታችን ለአዳም የገባለትን ከ5500 ዘመን በኃላ የሚፈፀመውን ከላይ የተገለፀውን የምህረት ስራ ከርቀት የሚያሳይ ነው::

ት ማለት ትህትና ነው:: ጌታችን አዳምን ሁሉ ሊያድነው በቀራንዮ መሰቀሉን ያመለክታል:: ትዕግስትም ነው:: እንዲሁም በ ታ የተጸጸተው አዳም ከታች ወደ ላይ መነሳቱንና በቴ መዳኑን ያሳያል።

ቶ ማለት ክርስቶስ ተነስቷል በአባቱም ቀኝ ተቀምጧል:: አዳም ዳግም ወደ ክብሩ ተመልሷል:: በስሙ ለሚያምኑት ለተጠሩት ልጅነትን ከኃይል ጋር ሰጣቸው:: የሰማይናንና የምድርንም መክፈቻ ቁልፍ ሰጣቸው:: በማለት አባቶች ያመሰጥሩታል::

2ኛ) ፊደላዊ ፍች፦

ተ ማለት ተሰብአ ወተሠገወ እማርያም እምቅድስት ድንግል ማለት ነው፡፡

ቱ ማለት መዝራዕቱ ለአብ ማለት ነው፡፡

ቲ ማለት ተአኳቲ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡

ታ ማለት ታው ትጉህ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡

ቴ ማለት ከሣቴ ብርሃን ማለት ነው፡፡

ት ማለት ትፍሥሕት ወሐሤት ማለት ነው፡፡

ቶ ማለት ነአምን ልደቶ ለክርስቶስ ማለት ነው።


ይቆየን!!!


ትክክለኛ ቻናሎች እነዚህ ናቸው


• የራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ ቻናሎች - 


? YouTube channel - Subscribe it now, thanks ❤️

namrud pictures & short films -https://youtube.com/channel/UCCW7MBWOARd2N_xupBoJAxw/videos


? የቴሌግራም ቻናላችን- አሁኑኑ join ያድርጉ 

@RAFATOEL ZETHIOPIA

(https://t.me/RAFATOEL_ZETHIOPIA)


?የፌስቡክ ገጻችን- አሁኑኑ Follow/Like  ያድርጉ 

ራፋቶኤል ዘኢትዮጵያ (https://facebook.com/events/542908322957973/)


?በድረገጻችን 

https://rafatoelzethiopia.websites.co.in


ይከተሉን subscribe እና join ያድርጉ እናመሰግናለን

This site was designed with Websites.co.in - Website Builder

WhatsApp Google Map

Safety and Abuse Reporting

Thanks for being awesome!

We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!

Have a great day!

Are you sure you want to report abuse against this website?

Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support